እንኳን ወደ Birlin Mühle Online-Shop ደህና መጡ

የ Birlin Mühle ትልቅ የኢትዮጲያ እና የኤርትርያ የምግብ ውጤቶች አቅራቢና አከፋፋይ ነው። የተለያዩ በአፍሪካዊ ባህላዊ መንገድ የተዘጋጁ ዱቄቶች በጥሩ ጥራት በኛ በኩል ያገኛሉ፣ ለዚህም ከ 100 ዓመታቶች በላይ ለአራት ትውልድ ሲተላለፍ የቆየው እና ያካበትነው ለምድ ምስክር ነው።የሐበሻ ምግቦች በቀጥታ ከአምራቹ

ከ 20 ዓመታቶች ጅምሮ ይህ የበተሰብ ድርጅታችን የሐበሻ ዱቄቶች በአውሮፓ ውስጥ ያከፋፍላል። ድርጁታችንም ትልቁ የኢትዮጲያ እና የኤርትርያ ባህላዊ ምርቶች አቅራቢ እና አከፋፋይ ነው።Birlin Mühle ከ 20 ዓመታቶች ጅምሮ በአውሮፓ ውስጥ የተለያዩ የሐበሻ ምግቦችን እና እንጀራ ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ ዱቄቶችን ያዘጋጃል ያከፋፈላል። ዛሬ አንዱ ትልቅ የኢትዮጲያ እና የኤርትርያ ምግብ አዘጋጅ እና አከፋፋይ ነን ። አንድ ምግብ ጣምናው የሚወሰነው በውስጡ ባለው ንጥረነገሮች እንደመሆኑ መጠን እኛም ለሙሉ ጣምናው በሙሉ ሀላፊነት እና በጥንቃቄ እናዘጋጃለን። ብዙ ደንበኞቻችን ከማመስገናቸውም በላይ አዳዲስ ተመጋቢዎችም በባህላዊ መንገድ የተቀመሙ የአፍሪካ ምግቦችን መውደድ ጀምረዋል።

ኢትዮጲያ እና ኤርትርያ ፦ የጥሩ ጣዕምና ምንጮች

አፍሪካ የተለያዩ ጣፋጭ ምግቦች እንዳላት የሚያውቊ ሰዎች ጥቂት ናቸው ። በተለይ ደግሞ ኢትዮጲያ እና ኤርትርያ ጣፋጭ እና የተለያዩ ጠቃሚ ንጥረነነሮችን የያዙዙ ምግቦች በማቅረብ የታወቊ ናቸው ። የሐበሻ ምግብ ከሚጠበቀው በላይ የተለያዩ አይነቶች እና አዘገጃጀቶች የያዘ ነው ።

  • እንጀራ ጥራት ካለው የጤፍ ዱቄት የሚዘጋጅ ሲሆን በእየእለቱ በማባያነት ያገለግላል ። ከቅርብ ጊዜ ጀምሮም በስፖርተኞች ዘንድ ተወዳጅነትን አግኝቷል።
  • የኢትዮጲያ በርበሬ ምንም እንኳን መሰረታዊ ቅመም ቢሆንም ከአውሮፒያን በርበሬ ጋር ሲነፃፀር ፍፁም በጥአምናው ወደር የለውም።
  • የተለያዩ እና ሙሉ መጋቢነት ያላቸው የአታክልት ምግቦች።
  • የተለያዩ ጣፋጭ የስጋ ምግቦች
  • ኢትዮጲያ የቡና ምንጭ እንደመሆንዋ ኢትዮጲያ ቡና
  • ኢትዮጲያ በተጨማሪም በማር ጠጅ አጠማመቅ ትታወቃለችአመጣጡ የተረጋገጠ ቁጥጥር እና ጥራት ያለው ምርት

ሁልጊዜም ከፍተኛ ጥራት ያለው ምርት ለደንበኞቻችን ለማቅረብ ምርቶቻችንን በቀጥታ ከአምራቾች እናስመጣለን። ይህንንም ጥራት ያለው ምርት ለማቅረብ በቦታው የእረጅም ጊዜ ልምድ ይጠይቃል። ስለዚህ ምርቶቻችንን የምናስመጣው የእኛን የጥራት መስፈር ከሚያሞአሉ አምራቾች ብቻ ነው ። በየጊዜውም ብቸኛ ከሆነ የምግብ ላብራቶር ምርቶቻችን ከምንም አይነት መበከል ነፃ መሆናቸውን እናስመረምራለን ።

ምርታችንን በየጊዜው እያሰፋን ነው።


* ተእታን ጨምሮ, በተጨማሪምያወጣል